ኢዮብ 39:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእርስዋ እንዳልሆኑ በልጆችዋ ላይ ትጨክናለች፤ ያለ ፍርሀትም በከንቱ ትሠራለች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእርሷ እንዳልሆኑ ሁሉ በልጆቿ ትጨክናለች፤ ድካሟም በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእርሷ ያልሆኑ ይመስል በልጆችዋ ትጨክናለች፥ ድካምዋ ከንቱም ሊሆን ቢችልም አትፈራም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጫጩቶችዋ የእርስዋ እንዳልሆኑ አድርጋ ትጨክንባቸዋለች፤ ድካምዋ ሁሉ በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእርስዋ እንዳልሆኑ በልጆችዋ ትጨክናለች፥ በከንቱም ብትሠራ አትፈራም፥ |
ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመልከት ማንን እንዲህ ቃረምህ? በውኑ ሴቶች የማኅፀናቸውን ፍሬ፥ ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?
ጋሜል። አራዊት እንኳ ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፤ የወገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኞች ሆኑ።