ኢዮብ 38:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባድማውንና ውድማውን ያጠግብ ዘንድ፥ ሣሩንም በምድረ በዳ ያበቅል ዘንድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባድማውንና በረሓውን መሬት የሚያጠግብ፣ ሣርም እንዲበቅልበት የሚያደርግ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣሩንም እንዲያበቅል፥ ማንም በሌለባት ምድር ላይ፥ ሰውም በሌለባት ምድረ በዳ ላይ ዝናብ እንዲዘንብ፥ ለፈሳሹ ውኃ መተላለፊያውን፥ ወይም ለሚያንጐደጉድ መብረቅ መንገድን ያበጀ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብ እንዲዘንብ የሚያደርግ ማነው? ጠፍና ባድማ የሆነውን መሬት ረስርሶ ምድሩንም ሣር እንዲያበቅል ያደረገው ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሣሩንም እንዲያበቅል፥ ማንም በሌለባት ምድር ላይ፥ ሰውም በሌለባት ምድረ በዳ ላይ ዝናብን ያዘንብ ዘንድ፥ ለፈሳሹ ውኃ መንዶልዶያውን፥ ወይስ ለሚያንጐደጕድ መብረቅ መንገድን ያበጀ ማን ነው? |