“ያች የተወለድሁባት ቀን ትጥፋ፥ ያችም፦ ወንድ ልጅ ነው ያሉባት ሌሊት።
“የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፤ ‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት።
“ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ እንዲሁም፦ ‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት።
ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም፦ ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ሌሊት።
እንዲህም አለ፦
ያች ቀን ጨለማ ትሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከታት፥ ብርሃንም አይብራባት።
እናቴ ሆይ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና ወዮልኝ! ለማንም አልጠቀምሁም፤ ማንም እኔን አልጠቀመኝም፤ ከሚረግሙኝም የተነሣ ኀይሌ አለቀ።