በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤
ኢዮብ 28:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአፈር ምክንያት እንደሚከፈል ወንዝ የጽድቅን መንገድ የረሱ በኀጢአታቸው ይደክማሉ። ከሰዎችም መካከል ይለያሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው እግር ረግጦት በማያውቅበት ስፍራ፣ ከሰዎች መኖሪያ ርቆ መውረጃ ጕድጓድ ይቈፍራል፤ ሰው በሌለበት ቦታ ይንጠላጠላል፤ ይወዛወዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ በመንገድኞችም ተረስተዋል፥ ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ከሚኖርበት ቦታ ርቀው፥ የሰው እግር ረግጦት ወደማያውቅ ስፍራ ይደርሳሉ። እዚያም ጥልቅ ጒድጓድ ይቈፍራሉ፤ በገመድም ላይ እየተንጠለጠሉ፥ ከሰው ተለይተው ብቻቸውን ይሠራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ ከሰውም እግር ተረሱ፥ ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ። |
በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤