“እግዚአብሔር ግን እነዚህን ለምን አልገሠጻቸውም? በምድር ላይ ሳሉ አላስተዋሉም፥ የቅንነት መንገድንም አላዩም። በአደባባይዋም አልሄዱም።
ኢዮብ 24:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጨለማ ቤቶችን ይነድላል፤ በቀን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንንም አያዩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጨለማ፣ ቤት ሰርስረው ይገባሉ፤ በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንንም አይፈልጉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቶቹን በጨለማ ይሰረስራሉ፥ በቀን ይሸሸጋሉ፥ ብርሃንም አያውቁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌቦች በሌሊት ቤት ሰርስረው ለስርቆት ይገባሉ፤ ቀን ግን ተሸሽገው ይውላሉ። ብርሃንንም ይጠላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቶቹን በጨለማ ይነድላሉ፥ በቀን ይሸሸጋሉ፥ ብርሃንም አያውቁም። |
“እግዚአብሔር ግን እነዚህን ለምን አልገሠጻቸውም? በምድር ላይ ሳሉ አላስተዋሉም፥ የቅንነት መንገድንም አላዩም። በአደባባይዋም አልሄዱም።
በመካከላቸውም የሚኖረው አለቃ በትከሻው ላይ አንግቶ በጨለማ ይወጣል፤ በዚያ ያወጡ ዘንድ ግንቡን ይነድላሉ፤ በዐይኑም ምድርን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።