La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 51:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እንግዲህ ጣዖቶቿን የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምድሯም ሁሉ፤ ቍስለኞች ያቃስታሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምቀጣበት በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጋው የሚያቃስትበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው። በባቢሎን ጣዖቶች ላይ የምፈርድበትና በሀገሪቱም የሚገኙ ቊስለኞች የጭንቀት ድምፅ የሚያሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋ የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጉት ያንቋርራሉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 51:52
6 Referencias Cruzadas  

እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።


ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን የባ​ቢ​ሎ​ንን ምስ​ሎች የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፤ ምድ​ር​ዋም ሁሉ ትደ​ር​ቃ​ለች፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም የሞ​ቱት ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይወ​ድ​ቃሉ።


ቸነ​ፈ​ር​ንም በአ​ንቺ ላይ፥ ደም​ንም በጎ​ዳ​ናሽ ላይ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ከዙ​ሪ​ያ​ሽም በላ​ይሽ ባለ ሰይፍ የተ​ወጉ በመ​ካ​ከ​ልሽ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አበ​ረ​ታ​ለሁ፤ ሰይ​ፌ​ንም በእጁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ግብ​ፅ​ንም ይወ​ጋ​በ​ታል፥ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ሰለ​ባ​ዋ​ንም ይሰ​ል​ባል።