ኤርምያስ 49:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ደነገጠች፤ ድምፅዋም እንደ ባሕር ድምፅ እነሆ ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውድቀታቸው ድምፅ ምድር ትናወጣለች፤ ጩኸታቸውም እስከ ቀይ ባሕር ያስተጋባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፥ የጩኸትም ድምፅ በኤርትራ ባሕር ተሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤዶም አወዳደቅ ዜና ሲሰማ ምድር ትናወጣለች፤ የድንጋጤውም ጩኸት ከዚያ አልፎ እስከ ቀይ ባሕር ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፥ የጩኸታቸውም ድምፅ በኤርትራ ባሕር ተሰማ። |
ብዙ አሕዛብን አስደንቅብሃለሁ፤ ሰይፌም በፊታቸው በተወረወረች ጊዜ ንጉሦቻቸው እጅግ አድርገው ይፈራሉ፤ በወደቅህባትም ቀን እያንዳንዱ ስለ ነፍሱ በየጊዜው ይንቀጠቀጣል።”
ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።