La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ያዕቆብ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእናንተ የተጠራውን ክቡር የሆነውን ስም የሚሳደቡ እነርሱ አይደሉምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ የምትጠሩበትን ያን ክቡር ስም የሚሰድቡስ እነርሱ አይደሉምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን?

Ver Capítulo



ያዕቆብ 2:7
23 Referencias Cruzadas  

በተነ፥ ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ይኖ​ራል፤ ቀን​ዱም በክ​ብር ከፍ ከፍ ይላል።


የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤ ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ።


በስሜ የተ​ጠ​ራ​ውን ለክ​ብ​ሬም የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን፥ የሠ​ራ​ሁ​ት​ንና ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ አምጣ” እለ​ዋ​ለሁ።


ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ።


ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።


በዘ​መ​ኑም ይሁዳ ይድ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተዘ​ልሎ ይቀ​መ​ጣል፤ ይህም ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያት ኢዮ​ሴ​ዴቅ ብሎ የጠ​ራው ነው።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።


ፈሪሳውያን ግን ሰምተው “ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም፤” አሉ።


“ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፤’ እንዳለ ትዝ አለን።


በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።


የቀ​ሩት ሰዎ​ችና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


በየ​ም​ኵ​ራቡ ሁሉ የማ​ስ​ገ​ደጃ ማዘዣ አም​ጥቼ፥ በግድ የኢ​የ​ሱ​ስን ስም እን​ዲ​ሰ​ድቡ ዘወ​ትር መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንም ወደ ሌሎች ከተ​ማ​ዎች እያ​ሳ​ደ​ድሁ ከፋ​ሁ​ባ​ቸው።


መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”


በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያሉ ነገ​ዶች ሁሉ ለሚ​ጠ​ሩት ለእ​ርሱ፤


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።


በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።


በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም አለው።