“ኤላምም በዚያ አለች፤ ኀይልዋም ሁሉ በመቃብርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል፤ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር ቅጣታቸውን አግኝተዋል።
ኢሳይያስ 38:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር የእግዚአብሔርን ማዳን፤ የእስራኤልንም መዳን በምድር ላይ አላይም፤ ከዘመዶችም ሰውን አላይም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አልሁ፤ “ዳግም እግዚአብሔርን፣ እግዚአብሔርን በሕያዋን ምድር አላይም፤ ከእንግዲህም የሰውን ዘር አላይም፤ በዚህ ዓለም ከሚኖሩትም ጋራ አልሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር ጌታን አላይም፤ በዓለምም የሚኖሩትን ሰዎች ከእንግዲህ አልመለከትም አልኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕያዋን በሚኖሩበት በዚህ ዓለም እግዚአብሔርን ወይም ከሕያው ፍጡር ሁሉ መካከል ሰውን ዳግመኛ አላይም ብዬ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፥ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም አልሁ። |
“ኤላምም በዚያ አለች፤ ኀይልዋም ሁሉ በመቃብርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል፤ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር ቅጣታቸውን አግኝተዋል።