ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ፤ የፈርዖን ሎሌዎችም ሁሉ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችም ሁሉ፥ የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፤
ዘፍጥረት 50:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ፥ ወንድሞቹም፥ የአባቱም ቤተ ሰቦች ወጡ፤ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን፥ ከብቶቻቸውንም ብቻ በጌሤም ተዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰዎች፣ ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰዎች በሙሉ ዐብረውት ሄዱ። በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍም ቤተሰቦች ሁሉ፥ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተሰቦች ወጡ፥ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተዉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የዮሴፍ ቤተሰቦች፥ ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተሰቦች ሁሉ ከዮሴፍ ጋር ሄዱ፤ በጌሴም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፥ በጎቻቸው፥ ፍየሎቻቸውና ከብቶቻቸው ብቻ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍም ቤተ ስቦች ሁሉ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተሰቦች ወጡ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተው። |
ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ፤ የፈርዖን ሎሌዎችም ሁሉ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችም ሁሉ፥ የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፤
ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤ አንድ ሰኰናም አይቀርም፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ከእነርሱ እንወስዳለንና፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንደምናመልከው ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም።”