ዘፍጥረት 46:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስቤር፤ የቤላ ልጆችም፤ ጌራ፥ ኖሔማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራድን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብንያም ልጆች፦ ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣ አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌን ሑፊምና አርድ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ ናዕማን አኪ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ። |
በዚያም አንድ ብንያማዊ የቢኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚባል የዐመፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እርሱም፥ “ከዳዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለንም፦ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ” ብሎ መለከት ነፋ።
ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በዘመኑ ሁሉ ይጋርደዋል፤ በትከሻውም መካከል ያድራል።