La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 42:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ያመጣ ዘንድ ከእ​ና​ንተ አን​ዱን ላኩ፤ እና​ንተ ግን እው​ነ​ትን የም​ት​ና​ገሩ ከሆነ ወይም ከአ​ል​ሆነ ነገ​ራ​ችሁ እስ​ኪ​ታ​ወቅ ድረስ ከዚህ ተቀ​መጡ፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ሰላ​ዮች ናችሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሉ፣ ከእናንተ አንዱን ላኩና ወንድማችሁን ይዞ ይመለስ፤ የቀራችሁት ግን የተናገራችሁት ቃል እውነትነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ እስር ቤት ትቈያላችሁ። እንደ ተናገራችሁት ካልሆነ ግን፣ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ሁላችሁም ሰላዮች ናችሁ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሉ፥ ከእናንተ አንዱን ላኩና ወንድማችሁን ይዞ ይመለስ፤ የቀራችሁት ግን የተናገራችሁት ቃል እስኪረጋገጥ ድረስ፥ እስር ቤት ትቆያላችሁ። እንደ ተናገራችሁት ካልሆነ ግን፥ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ሁላችሁም ሰላዮች ናችሁ” አላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ነገራችሁ ይፈተን ዘንድ ከእናንተ አንዱን ስደዱ፥ ወንድማችሁንም ይዞ ይምጣ እናንተም ታድራችሁ ተቀመጡ ይህ ካልሆነ የፈርዖን ሕይወት ሰላዮች ናችሁ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 42:16
4 Referencias Cruzadas  

እኛ ሁላ​ችን የአ​ንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የሰ​ላም ሰዎች ነን፤ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህስ ሰላ​ዮች አይ​ደ​ሉም።”


“የሀ​ገሩ ጌታ የሆ​ነው ሰው በክፉ ንግ​ግር ተና​ገ​ረን፤ የም​ድ​ሪ​ቱም ሰላ​ዮች እን​ደ​ሆን አድ​ርጎ ወደ እስር ቤት አስ​ገ​ባን።”


የአ​ሞ​ንም ልጆች አለ​ቆች ጌታ​ቸ​ውን ሐኖ​ንን፥ “ዳዊት አባ​ት​ህን በፊ​ትህ ለማ​ክ​በር አጽ​ና​ኞ​ችን ወደ አንተ የላከ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ዳዊ​ትስ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ሰ​ለል፥ ለመ​ፈ​ተ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን የላከ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት።


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድ​ሪ​ቱን ኢያ​ሪ​ኮን እዩ” ብሎ ከሰ​ጢም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሰላ​ዮ​ችን በስ​ውር ላከ። እነ​ዚ​ያም ሁለት ጐል​ማ​ሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደ​ሚ​ሉ​አ​ትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚ​ያም ዐደሩ።