ቴምናሕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ዕቅብት ነበረች፤ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፤ የዔሳውም ሚስት የሐዳሶ ልጆች እነዚህ ናቸው።
ዘፍጥረት 36:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆሬ መስፍን፥ ጎቶን መስፍን፥ አማሌቅ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህ የሓዳሶ ልጆች ናቸው ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቆሬ አለቃ፥ ገዕታም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቆሬ፥ ገዕታምና ዐማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም የኤልፋዝ ነገድ አለቆች ሲሆኑ፥ እነርሱም ዔሳው ከሚስቱ ከዓዳ የወለዳቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኮሬ አለቃ ጎቶም አለቃ አማሌቅ አለቃ በኤዶም ምድር የኤልፋእ አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው። |
ቴምናሕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ዕቅብት ነበረች፤ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፤ የዔሳውም ሚስት የሐዳሶ ልጆች እነዚህ ናቸው።
የዔሳው ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስፍን፥ ኦሜር መስፍን፥ ሳፍር መስፍን፥ ቄኔዝ መስፍን፥
የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ናሖት መስፍን፥ ዛራ መስፍን፥ ሲን መስፍን፥ ሞዛህ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው።