እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን እጅግ ቈስለው ሳሉ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ተደፋፍረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፤
ዘፍጥረት 34:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ፤ እኅታቸው ዲናንም ከሴኬም ቤት ይዘው ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤሞርንና ሴኬምንም በሰይፍ ገድለው፣ እኅታቸውን ዲናን ከሴኬም ቤት አውጥተው ይዘዋት ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ፥ እኅታቸውን ዲናንም ከሴኬም ቤት ይዘው ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሞርንና ልጁን ሴኬምን ሳይቀር በሰይፍ ከገደሉ በኋላ፥ ዲናን ከሴኬም ቤት ወስደው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዱንም ሁሉ ገደሉ ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ እኅታቸውን ዲናንም ከሴኬም ቤት ይዘው ወጡ። |
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን እጅግ ቈስለው ሳሉ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ተደፋፍረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፤
አበኔርም ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “ሰይፍ ለድል የምታጠፋ አይደለምን? ፍጻሜዋስ መራራ እንደ ሆነ አታውቅምን? ሕዝቡ ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ ይመለሱ ዘንድ ሕዝቡን የማትናገር እስከ መቼ ነው?”
አሦርም ይወድቃል፤ የሚወድቀውም በሰው ሰይፍ አይደለም፤ የምትበላቸውም የሰው ሰይፍ አይደለችም፤ የሚሸሹም ከሰይፍ ፊት አይደለም ጐልማሶቻቸው ግን ይሸነፋሉ።
በሰይፍ ስለት ይወድቃሉ፤ በአሕዛብም ሁሉ ይማረካሉ፤ የአሕዛብ ጊዜያቸው እስኪፈጸም ድረስ አሕዛብ ኢየሩሳሌምን ይረግጡአታል።