La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 30:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዛሬ በጎ​ችህ ሁሉ ይለፉ፤ በዚ​ያም ከበ​ጎ​ችህ መካ​ከል ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ ያለ​በ​ትን ጥቁ​ሩ​ንም በግ ሁሉ፥ ከፍ​የ​ሎ​ቹም ነቍ​ጣና ዝን​ጕ​ር​ጕር ያለ​በ​ትን ለይ​ልኝ፤ እነ​ር​ሱም ደመ​ወዜ ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመንጎቹ መካከል ዛሬ ልዘዋወርና ከበጎቹ መካከል ዝንጕርጕር የሆኑትን፣ ነቍጣ ያለባቸውንና ጥቋቍሮቹን እንዲሁም ከፍየሎቹ ነቍጣ ያለባቸውንና ዝንጕርጕሮቹን ልምረጥ፤ እነዚህ ደመወዜ ይሁኑ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቁጣና ዝንጉርጉር ያለበቱን እለያለሁ፥ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጒርጒርና ነቊጣ፥ ጥቊርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቊጣና ዝንጒርጒር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጉርጉርና ነቍጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር እለያለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 30:32
5 Referencias Cruzadas  

ላባም፥ “የም​ሰ​ጥህ ምን​ድን ነው?” አለው። ያዕ​ቆ​ብም አለው፥ “ምንም አት​ስ​ጠኝ፤ ይህ​ንም ነገር ብታ​ደ​ር​ግ​ልኝ እን​ደ​ገና በጎ​ች​ህን አሰ​ማ​ራ​ለሁ፤ እጠ​ብ​ቃ​ለ​ሁም።


ስለ​ዚ​ህም በፊ​ትህ ያለ​ውን ደመ​ወ​ዜን ለመ​መ​ል​ከት በመ​ጣህ ጊዜ ወደ​ፊት ጻድ​ቅ​ነ​ቴን ይመ​ሰ​ክ​ር​ል​ኛል፤ ከፍ​የ​ሎች ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ የሌ​ለ​በት፥ ከበግ ጠቦ​ቶ​ችም ጥቁር ያል​ሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰ​ረቀ ይቈ​ጠ​ር​ብኝ።”


በዚ​ያም ቀን ከተ​ባ​ቶቹ ፍየ​ሎች ሽመ​ል​መሌ መሳ​ይና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከእ​ን​ስ​ቶቹ ፍየ​ሎች ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ ያለ​ባ​ቸ​ውን፥ ነጭ ያለ​በ​ትን ማን​ኛ​ው​ንም ሁሉ፥ ከበ​ጎ​ቹም መካ​ከል ጥቁ​ሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለል​ጆቹ ሰጣ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በጎቹ በሚ​ፀ​ንሱ ጊዜ ዐይ​ኔን አን​ሥቼ በሕ​ልም አየሁ፤ እነ​ሆም፥ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።


ደመ​ወ​ዝህ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮቹ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችን ወለዱ፤ ነጫ​ጮቹ ደመ​ወ​ዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ነጫ​ጮ​ችን ወለዱ።