Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 30:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በመንጎቹ መካከል ዛሬ ልዘዋወርና ከበጎቹ መካከል ዝንጕርጕር የሆኑትን፣ ነቍጣ ያለባቸውንና ጥቋቍሮቹን እንዲሁም ከፍየሎቹ ነቍጣ ያለባቸውንና ዝንጕርጕሮቹን ልምረጥ፤ እነዚህ ደመወዜ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቁጣና ዝንጉርጉር ያለበቱን እለያለሁ፥ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጒርጒርና ነቊጣ፥ ጥቊርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቊጣና ዝንጒርጒር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ዛሬ በጎ​ችህ ሁሉ ይለፉ፤ በዚ​ያም ከበ​ጎ​ችህ መካ​ከል ዝን​ጕ​ር​ጕ​ርና ነቍጣ ያለ​በ​ትን ጥቁ​ሩ​ንም በግ ሁሉ፥ ከፍ​የ​ሎ​ቹም ነቍ​ጣና ዝን​ጕ​ር​ጕር ያለ​በ​ትን ለይ​ልኝ፤ እነ​ር​ሱም ደመ​ወዜ ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጉርጉርና ነቍጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር እለያለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 30:32
5 Referencias Cruzadas  

ላባም፣ “ታዲያ ምን ልስጥህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ምንም አትስጠኝ፤ ነገር ግን የምጠይቅህን አንዲት ነገር ብቻ ብታደርግልኝ ከብቶችህን ማገዴን እቀጥላለሁ፤


ወደ ፊት ደመወዜን ለመቈጣጠር በምትመጣበት ጊዜ ታማኝነቴ ይታወቃል፤ በመንጎቼ መካከል ዝንጕርጕር ወይም ነቍጣ የሌለበት ፍየል ወይም ጥቍር ያልሆነ በግ ቢገኝ ያ እንደ ተሰረቀ ይቈጠር።”


ነገር ግን በዚያ ዕለት ከተባዕት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቍጣ ያለባቸውን ሁሉ፣ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቍጣ ያለባቸውን ዝንጕርጕር የሆኑትን ሁሉ፣ ማንኛውንም ነጭ ያለበትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቍር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው።


“እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ።


እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos