ዘፍጥረት 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይህያንም ልጆች ኤልሳ፥ ተርሴስ፥ ኬቲም፥ ሮድኢ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዋን ልጆች፦ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዋን ልጆች፦ የኤሊሻ፥ የተርሴስ፥ የኪቲምና የሮዳኒም ሰዎች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዋን ልጆች፦ የኤሊሻ፥ የተርሴስ፥ የኪቲምና የሮዳኒም ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው። |
ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና።
እርሱም፥ “አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደስ አይበልሽ፤ ተነሥተሽ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፤ በዚያም ደግሞ አታርፊም” አለ።
“ከኀይልሽ ሁሉ ብዛት የተነሣ የተርሴስ ሰዎች ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ገበያሽን ብር፥ ወርቅና ብረት፥ ቆርቆሮና እርሳስም አደረጉ።
ከባሳን ኮምቦል መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፤ መቅደስሽንም በዝኆን ጥርስ ሠሩ፤ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍም ቤቶችሽን ሠርተዋል።
ዓላማ እንዲሆንልሽ ሸራሽ ከግብፅ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፤ መደረቢያሽም ከኤሊሳ ደሴቶች ሰማያዊና ቀይ ሐር ተሠርቶአል።