በአዕማዱም ራስ ላይ የነበሩትን ጕልላቶች ይሸፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መርበብ ሥራ አደረገ፤ አንዱም መርበብ ለአንዱ ጕልላት፥ ሁለተኛውም መርበብ ለሁለተኛው ጕልላት ነበረ።
ዘፀአት 28:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልብሰ እንግድዓውም የተጐነጐኑትን ቋዶች እንደ ገመድ አድርገህ ከጥሩ ወርቅ ሥራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለደረት ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ ሆኖ የተጌጠ ጕንጕን አብጅለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለደረት ኪሱም የተጎነጎኑትን ድሪዎች እንደ ገመድ አድርገህ ከንጹሕ ወርቅ ሥራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለደረት ኪሱም እንደ ገመድ የተጐነጐነ ድሪ ከንጹሕ ወርቅ ሥራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደረቱ ኪስም የተጎነጎኑትን ድሪዎች እንደ ገመድ አድርገህ ከጥሩ ወርቅ ሥራቸው። |
በአዕማዱም ራስ ላይ የነበሩትን ጕልላቶች ይሸፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መርበብ ሥራ አደረገ፤ አንዱም መርበብ ለአንዱ ጕልላት፥ ሁለተኛውም መርበብ ለሁለተኛው ጕልላት ነበረ።
ሮማኖችንም ሠራ፤ በአንድ ጕልላት ዙሪያ በሁለት ተራ፥ በአንድም መርበብ ላይ ሁለት ተራ ነበረ፤ እንዲሁም ለሁለተኛው ጕልላት አደረገ።
ሁለት ቋዶችንም ከጥሩ ወርቅ እንደ ተጐነጐነ ገመድ አድርገህ ሥራ፤ የተጐነጐኑትንም ቋዶች በፈርጦቹ ላይ አንጠልጥል።
የዕንቍም ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ በየስማቸውም ማኅተም አቀራረጽ ይቀረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶችም ይሁኑ።
ለልብሰ እንግድዓውም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፤ ሁለቱንም ቀለበቶች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገን አድርጋቸው።