ቤርሳቤህም በግንባርዋ በምድር ላይ ተደፍታ ለንጉሡ ሰገደችና፥ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘለዓለም በሕይወት ይኑር” አለች።
ኤፌሶን 5:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲያስ እናንተም ሁላችሁ እንዲሁ ሚስቶቻችሁን እንደ ራሳችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባልዋን ትፍራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባሏን ታክብር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም ከእናንተ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ይህ ነገር እናንተንም ይመለከታል፤ ስለዚህ ባል ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ። |
ቤርሳቤህም በግንባርዋ በምድር ላይ ተደፍታ ለንጉሡ ሰገደችና፥ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘለዓለም በሕይወት ይኑር” አለች።
ወንዶችም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት፥ ራሱንም ስለ እርስዋ ቤዛ አድርጎ እንደ ሰጠላት ሚስቶቻቸውን ይውደዱ።
በሥጋ የወለዱን አባቶቻችን የሚቀጡን፥ እኛም የምንፈራቸው ከሆነ፥ እንግዲያ ይልቁን ለመንፈስ አባታችን ልንታዘዝና ልንገዛ በሕይወትም ልንኖር እንዴት ይገባን ይሆን?