La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 32:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፤ ምግ​ባ​ርና ሃይ​ማ​ኖት የላ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አእምሮ የጐደላቸው፣ ማስተዋልም የሌላቸው ሕዝብ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የእስራኤል ሕዝብ አእምሮ ቢሶች ናቸው፤ አያስተውሉምም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ 2 ማስተዋልም የላቸውም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 32:28
12 Referencias Cruzadas  

ሰው​ንም፦ ‘እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራ​ቅም ማስ​ተ​ዋል ነው’ ” አለው።


የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።


ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድ​ጋሚ እን​ዲ​ፈ​ልስ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ የጥ​በ​በ​ኞ​ች​ንም ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ተ​ዋ​ዮ​ች​ንም ማስ​ተ​ዋል እሰ​ው​ራ​ለሁ።”


የሕ​ዝቤ አለ​ቆች አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ እነ​ርሱ ሰነ​ፎች ልጆች ናቸው፤ ማስ​ተ​ዋ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ክፉ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ ብል​ሃ​ተ​ኞች ናቸው፤ በጎ ነገ​ርን ማድ​ረግ ግን አያ​ው​ቁም።


ጥበ​በ​ኞች አፍ​ረ​ዋል፤ ደን​ግ​ጠ​ው​ማል፤ ተማ​ር​ከ​ው​ማል፤ እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጥለ​ዋል፤ ምን ዓይ​ነት ጥበብ አላ​ቸው?


ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


የዚህ ዓለም ጥበብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ቍ​ርና ነውና፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “ጠቢ​ባ​ንን የሚ​ገ​ታ​ቸው ተን​ኰ​ላ​ቸው ነው።”


ደን​ቆሮ፥ ብል​ሃ​ተ​ኛም ያል​ሆ​ንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ትመ​ል​ሳ​ለ​ህን? የፈ​ጠ​ረህ አባ​ትህ አይ​ደ​ለ​ምን? የፈ​ጠ​ረ​ህና ያጸ​ናህ እርሱ ነው።