La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 3:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ እን​ድ​ሻ​ገ​ርና፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ያለ​ች​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር፥ ያንም መል​ካ​ሙን ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር አንጢ ሊባ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳይ ፍቀ​ድ​ልኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ከዮርዳኖስ ማዶ ያለችውን ያችን መልካሚቱን ምድር፣ ውብ የሆነችውን ኰረብታማ አገርና ሊባኖስን እንዳይ ፍቀድልኝ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እለምንሃለሁ፥ ልሻገር፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጌታ ሆይ! የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሬ ከወንዙ ማዶ ያለችውን ውብና ኮረብታማ የሆነችውን ለምለሚቱን ምድርና የሊባኖስን ተራራ ማየት እንድችል ፍቀድልኝ።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ ልሻገር፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 3:25
6 Referencias Cruzadas  

ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ።


በዚያ ቀን ከግ​ብፅ ምድር ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው፥ ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ት​በ​ልጥ ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጄን አነ​ሣሁ።


እኛስ በአ​ንተ ዘንድ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ርስት አድ​ር​ገህ ስጠን፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን አታ​ሻ​ግ​ረን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ አል​ሰ​ማ​ኝ​ምም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘ይበ​ቃ​ሃል፤ በዚህ ነገር ደግ​መህ አት​ና​ገ​ረኝ።’