La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 28:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ግ​ርህ በታች ይወ​ድቁ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህን ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ በሰ​ባ​ትም መን​ገድ ከፊ​ትህ ይሸ​ሻሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ጌታ በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ጠላቶችህ በአንተ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ድል ያደርግልሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ይሸሻሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 28:7
21 Referencias Cruzadas  

በጨ​ለ​ማም ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ሰፈር መጀ​መ​ሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጠ፤ ደግ​ሞም ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ተራ​ራ​ማው እስከ ኤፍ​ሬም ሀገር ድረስ ወደ ሕዝቡ ወጥቶ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መለ​ሳ​ቸው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።


አን​ተም በመ​ግ​ባ​ትህ ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ፥ በመ​ው​ጣ​ት​ህም ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን በአ​ንተ ላይ፥ በጎ​ተ​ራህ፥ በእ​ህ​ል​ህም ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ወ​ርድ ይል​ካል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥ​ህም ምድር ይባ​ር​ክ​ሃል።


አንዱ ሽሁን እን​ዴት ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል? ሁለ​ቱስ ዐሥ​ሩን ሽህ እን​ዴት ያባ​ር​ሩ​አ​ቸ​ዋል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍዳ​ውን አም​ጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና። አም​ላ​ካ​ች​ንም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረን ስለ እና​ንተ የሚ​ዋጋ እርሱ ነውና ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳ​ድ​ዳል።


እነ​ዚ​ያም ከከ​ተማ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሠራ​ዊት መካ​ከ​ልም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እኒያ ከወ​ዲያ፥ እኒ​ህም ከወ​ዲህ ሆነው አንድ እን​ኳን ሳይ​ቀ​ርና ሳያ​መ​ልጥ ገደ​ሉ​አ​ቸው።