ዘዳግም 23:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእናንተ ውስጥ ሌሊት በሚሆነው ርኵሰት የረከሰ ሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈርም አይግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር፣ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቈይ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ መካከል ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፥ እዚያው ይቆይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ሌሊት በሕልሙ ከአባለ ዘሩ የፈሰሰ እርጥበት በሰውነቱ ላይ ቢገኝ ከሰፈር ወጥቶ በዚያው ይቈይ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእናንተ መካከል ሌሊት በሚሆነው ርኩሰት የረከስ ሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፥ ወደ ሰፈርም አይግባ። |
እናንተ ግን እርም ብለን ከተውነው እንዳትወስዱ ተጠንቀቁ፤ ከእርሱም ተመኝታችሁ አትውሰዱ፤ ብትወስዱ ግን የእስራኤልን ሰፈር የተረገመች ታደርጓታላችሁ፤ እኛንም ታጠፉናላችሁ።