ዘዳግም 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነውር ነገርም ቢያመጣባት፥ እኔ ይህችን ሴት ሚስቴ አድርጌ አገባኋት፤ በደረስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም ብሎ ክፉ ስም ቢያወጣባት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሟንም በማጥፋት፣ “ይህችን ሴት አገባኋት፤ ዳሩ ግን በደረስሁባት ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁም” ቢል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነውር ነገር አውርቶ፦ ‘እኔ ይህችን ሴት ሚስት አድርጌ አገባኋት፥ በደርስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም’ ብሎ በክፉ ስም ቢያሳጣት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ይህችን ሴት አግብቼ ክብረ ንጽሕናዋን አላገኘሁም’ ብሎ በሐሰት ክስ ስምዋን ቢያጠፋ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነውር ነገር አውርቶ፦ እኔ ይህችን ሴት ሚስት አድርጌ አገባኋት፥ በደርስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም ብሎ በክፉ ስም ቢያሳጣት፥ |
የብላቴናዪቱ አባትና እናት የልጃቸውን የድንግልናዋን ልብስ ወስደው በበሩ አደባባይ ወደ ተቀመጡ ወደ ከተማ ሽማግሌዎች ያምጡት፤
በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል ያስከፍሉት፤ ለብላቴናዪቱም አባት ይስጡት፤ እርስዋም ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።
እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤