በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤
ዘዳግም 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቈጠረ፤ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበረ፤ አሞናውያን ግን “ዘምዞማውያን” ብለው ይጠሩአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ደግሞ በዚያ ይኖሩ የነበሩት የራፋይማውያን ምድር እንደ ሆነ ይቈጠር ነበር፤ አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ፥ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሩአቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም [ይህም ግዛት በዚያ ይኖሩ በነበሩ ሕዝብ ይጠሩ በነበሩበት ስም የረፋያውያን ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ዐሞናውያን በበኩላቸው ዛምዙሚም ብለው ይጠሩአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ፤ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሩአቸዋል። |
በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤
እነርሱም እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ፥ ጽኑዓንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ።
ከራፋይንም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።