ቈላስይስ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልንጀሮቻችሁን ታገሡአቸው፤ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ፤ ባልንጀሮቻችሁን የነቀፋችሁበትን ሥራ ተዉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እንዲሁ አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ማንም ሰው በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ ይቅር በሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤ |
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
እኛም የበደለንን ሁሉ ይቅር እንድንል በደላችንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ።”
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን ኣያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ፤ በልብሱም ላይ ዕጣ ተጣጣሉና ተካፈሉ።
ይቅር የምትሉት ቢኖር፥ እኔም ከእናንተ ጋር ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ያልሁትን በክርስቶስ ፊት ስለ እናንተ ይቅር ብያለሁ።
በፍጹም የዋህነት ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ እየታገሣችሁ፥ ለወንድሞቻችሁም እሺ እያላችሁ፥ በፍቅር እየተጋችሁና እየተባበራችሁ፥
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ መረጣቸው ቅዱሳንና ወዳጆች፥ ምሕረትንና ርኅራኄን፥ ቸርነትንና ትሕትናን፥ የውሀትንና ትዕግሥትን ልበሱት።