ሐዋርያት ሥራ 27:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋ ጊዜም ቀዛፊዎች ቦታውን አልለዩም፤ የሚሄዱበትንም አላወቁም፤ ነገር ግን ለባሕሩ አቅራቢያ የሆነውን የደሴት ተራሮች አዩ፤ መርከባቸውንም ወደ እዚያ ሊያስጠጉ ፈለጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በነጋም ጊዜ፣ ወደ የብስ መቅረባቸውን አላወቁም ነበር፤ ነገር ግን ዳር ዳሩ አሸዋማ የሆነ የባሕር ሥርጥ አይተው፣ ቢቻላቸው መርከቡን ገፍተው ወደዚያ ለማድረስ ወሰኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋም ጊዜ ምድሩን አላወቁትም፤ ነገር ግን የአሸዋ ዳር ያለውን የባሕር ሰርጥ ተመለከቱ፤ ቢቻላቸውም መርከቡን ወደዚያ ይገፉ ዘንድ ቆረጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነጋም ጊዜ የደረሱበትን ቦታ አላወቁትም፤ ነገር ግን የአሸዋ ዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ የሚቻል ቢሆን መርከቡን ወደዚያ በመግፋት ወደ ዳር ለማውጣት አሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋም ጊዜ ምድሩን አላወቁትም፥ ነገር ግን የአሸዋ ዳር ያለውን የባሕር ስርጥ ተመለከቱ፥ ቢቻላቸውም መርከቡን ወደዚያ ይገፉ ዘንድ ቈረጡ። |
መልሕቁንም ፈትተው በባሕር ላይ ጣሉት፤ የሚያቆሙበትንም አመቻችተው እንደ ነፋሱ አነፋፈስ መጠን ትንሹን ሸራ ሰቀሉ፤ ወደ ባሕሩ ዳርቻም ሄድን።