ሐዋርያት ሥራ 14:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በርናባስን ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም የትምህርቱ መሪ እርሱ ነበርና ሄርሜን ብለው ጠሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርናባስን “ድያ” አሉት፤ ጳውሎስም ዋና ተናጋሪ ስለ ነበር “ሄርሜን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በርናባስንም “ድያ” አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ “ሄርሜን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በርናባስንም “ድያ” አሉት፤ ዋናው ተናጋሪ ጳውሎስ ስለ ነበረ እርሱን “ሄርሜን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት። |
በከተማውም ፊት ለፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባ አክሊሎችን ወደ ደጃፍ አመጣ፤ ከሕዝቡም ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ።
ከዚህም በኋላ የከተማው ጸሓፊ ተነሥቶ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፥ ስሙ፤ የኤፌሶን ከተማ ታላቂቱን አርጤምስንና ከሰማይ የወረደውን ጣዖትዋን እንደምትጠብቅ የማያውቅ ማነው?