አበኔርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብላቴኖቹም አንድ ጐልማሳ ያዝ፤ መሣሪያውንም ለራስህ ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።
2 ሳሙኤል 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም አሣሄልን፥ “ከምድር ጋር እንዳላጣብቅህ እኔን ከማሳደድ ፈቀቅ በል፤ ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ፊቴን አቅንቼ አይ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል? እንደዚህ አይሆንምና ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ተመለስ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም አበኔር አሣሄልን፣ “እኔን መከታተል ብትተው ይሻልሃል፤ እኔስ ለምን ከመሬት ጋራ ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት ቀና ብዬ እንዴት አያለሁ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገናም አበኔር፥ “እኔን ማሳደድህን ተው! እኔስ ስለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ብዬ አያለሁ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም አበኔር “እኔን ማሳደድህን ተው! ለምን እንድገድልህ ትገፋፋኛለህ? አንተንስ ብገድል የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ማየት እችላለሁ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም አሣሄልን፦ ከምድር ጋር እንዳላጣብቅህ እኔን ከማሳደዱ ፈቀቅ በል፥ ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ፊቴን አቅንቼ አይ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል? አለው። |
አበኔርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብላቴኖቹም አንድ ጐልማሳ ያዝ፤ መሣሪያውንም ለራስህ ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም።
ሳኦልም ሜልኮልን አላት፥ “ስለምን እንዲህ አታለልሽኝ? ጠላቴን አስኰበለልሽ፤ እንዲያመልጥም አደረግሽው?” ሜልኮልም ለሳኦል፥ “እርሱ፦ አውጥተሽ ስደጂኝ፤ አለዚያ እገድልሻለሁ አለኝ” አለችው።