የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋው አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጐድልም።”
2 ነገሥት 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ልጆችዋን፥ “ደግሞ ማድጋ አምጡልኝ” አለቻቸው፤ እነርሱም፥ “ሌላ ማድጋ የለም” አሏት፤ ዘይቱም ቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማድጋዎቹ ሁሉ ከሞሉ በኋላ ልጇን፣ “ሌላ ማድጋ አምጣ” አለችው። እርሱ ግን፣ “ምንም የቀረ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም ዘይቱ መውረዱን አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማድጋዎቹም በሞሉ ጊዜ ልጅዋን “ደግሞም ማድጋ አምጣልኝ፤” አለችው፤ እርሱም “ሌላ ማድጋ የለም፤” አላት፤ ዘይቱም ቆመ። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋው አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጐድልም።”
የእግዚአብሔርም ሰው አዝኖ፥ “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ቢሆን ኖሮ ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በመታኻቸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ” አለ።
እንዲሁም ከእርሱ ሄዳ፥ በሩን ከእርስዋና ከልጆችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነርሱም ማድጋዎቹን ወደ እርስዋ ያቀርቡላት ነበር፤ እርስዋም ትገለብጥ ነበር።
ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ከቍርስራሹ ምንም የሚወድቅ እንዳይኖር የተረፈውን ቍርስራሽ አንሡ፤” አላቸው።
በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ዳግመኛ መና አላገኙም፤ በዚያው ዓመት የፊኒቆንን ምድር ፍሬ ሰበሰቡ።