በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በኤማት ምድር ባለችው በዴብላታ አሰረው፤ በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት።
2 ነገሥት 25:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአበዛዎቹም አለቃ ናቡዛርዳን ማርኮ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ዴብላታ አመጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ናቡዘረዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ነበረበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናቡዛርዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ በሐማት ግዛት በምትገኘው በሪብላ ከተማ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወሰዳቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡዛርዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ በሐማት ግዛት በምትገኘው በሪብላ ከተማ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወሰዳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። |
በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በኤማት ምድር ባለችው በዴብላታ አሰረው፤ በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት።
በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
ዔ። የእግዚአብሔር ፊት ክፍላቸው ነበረ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፤ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፤ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።