ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በዓልም አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
2 ቆሮንቶስ 6:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክርስቶስን ከቤልሆር ጋር አንድ የሚያደርገው ማን ነው? ወይስ ምእመናንን ከመናፍቃን ጋር አንድ ወገን የሚያደርጋቸው ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክርስቶስ ከቤልሆር ጋራ ምን ስምምነት አለው? የሚያምን ከማያምን ጋራ ምን ኅብረት አለው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን ስምምነት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክርስቶስና ዲያብሎስ እንዴት ሊስማሙ ይችላሉ? የሚያምንና የማያምንስ በምን ሊወዳጁ ይችላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? |
ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በዓልም አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
ዘሩባቤልና ኢያሱም፥ የቀሩትም የእስራኤል አባቶች ቤቶች አለቆች፥ “የአምላካችንን ቤት መሥራት ለእኛና ለእናንተ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ግን የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቤት እንሠራለን” አሉአቸው።
ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት።
“አሁንም በገባዖን ውስጥ የበደሉ የዐመፅ ሰዎችን እንድንገድላቸው አውጥታችሁ ስጡን፤ ከእስራኤልም ልጆች ክፋትን እናርቃለን።” የብንያም ልጆች ግን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አልወደዱም።