ንጉሡም በይሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከንጉሡ ከአርተሰስታ ከሃያኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወንድሞች ለአለቃ የሚገባውን ቀለብ አልበላንም።
2 ቆሮንቶስ 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ ቲቶን ማለድሁት፤ ከእርሱም ጋር ሌላውን ወንድማችንን ላክሁት፤ በውኑ ቲቶ የበደላችሁ በደል አለን? በእርሱ በአደረው መንፈስ የምንመላለስ፥ እርሱም የሄደበትን ፍለጋ የምንከተል አይደለንምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንሁት፤ ወንድማችንንም ከርሱ ጋራ ላክሁት። ቲቶ በዘበዛችሁን? ከርሱ ጋራ በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቲቶን ገፋፋሁት፤ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ ለራሱ ጥቅም አውሏችኋልን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አንድ ዓይነት እርምጃስ አልወሰድንምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንኩት፤ ያንን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ላክሁት፤ ታዲያ፥ ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? እኔና እርሱ ያገለገልናችሁ በአንድ መንፈስ አልነበረምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቲቶን መከርሁት ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ አታለላችሁን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? በአንድ ፍለጋስ አልተመላለስንም? |
ንጉሡም በይሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከንጉሡ ከአርተሰስታ ከሃያኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወንድሞች ለአለቃ የሚገባውን ቀለብ አልበላንም።
ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግዚአብሔርንም አለው፥ “ወደ መሥዋዕታቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንዳችም ተመኝቼ አልወሰድሁም፤ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”
ለተገዘሩትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተገዘሩት ብቻ አይደለም፤ እርሱ አባታችን አብርሃም ሳይገዘር እንደ አመነ ሳይገዘሩ የአባታችን የአብርሃምን የሃይማኖቱን ፍለጋ ለሚከተሉ ደግሞ ነው እንጂ።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ታገሡን፥ የበደልነው የለም፤ የገፋነውም የለም፤ ያጠፋነውም የለም፤ የቀማነውም የለም።