ገባዖናዊው ሰማያስ፥ እርሱ በሠላሳው መካከልና በሠላሳው ላይ ኀያል ሰው ነበረ፤ ኤርምያስ፥ ሕዝኤል፥ ዮሐናን፥ ገድሮታዊ ዮዛባት፤
2 ዜና መዋዕል 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በምታንያስ ልጅ በኢያሔል ልጅ በብልአንያ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በኡዝሔል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የአሳፍ ዘር በሆነው በሌዋዊው በዘካርያስ ልጅ፣ በየሕዚኤል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መጣ። ዘካርያስም የበናያስ ልጅ ሲሆን፣ በናያስም የመታንያን ልጅ የሆነው የይዒኤል ልጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ በይዒኤል ልጅ በበናያስ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በየሕዝኤል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሕዝቡ ጋር በነበረ በአንድ ሌዋዊ ላይ ወረደ፤ ይህም ሌዋዊ ያሐዚኤል ተብሎ የሚጠራ የዘካርያስ ልጅ ነበር፤ እርሱም በማታንያ፥ በይዒኤልና በበናያ በኩል ደግሞ የአሳፍ ወገን ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ፥ በይዒኤል ልጅ፥ በበናያስ ልጅ፥ በዘካርያስ ልጅ በየሕዝኤል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤ |
ገባዖናዊው ሰማያስ፥ እርሱ በሠላሳው መካከልና በሠላሳው ላይ ኀያል ሰው ነበረ፤ ኤርምያስ፥ ሕዝኤል፥ ዮሐናን፥ ገድሮታዊ ዮዛባት፤
የእግዚአብሔርም መንፈስ በካህኑ በኢዮአዳ ልጅ በአዛርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት ቆመና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካምም አይሆንላችሁም፤ እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁ እርሱ ትቶአችኋል” አላቸው።
ያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ፤ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ይልሃል። የዐመፅ እስራትን ከመካከልህ ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ማንጐራጐርንም ብትተው፥
ወደእርሱም ተመልክቶ ፈራና፥ “አቤቱ፥ ምንድን ነው?” አለ፤ መልአኩም እንዲህ አለው፥ “ጸሎትህም ምጽዋትህም መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጎአል።