Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 10:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጸሎ​ትህ ተሰማ፤ ምጽ​ዋ​ት​ህም ታሰ​በ​ልህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እንዲህ አለኝ፤ ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፤ ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ምጽዋትህም ለመታሰቢያነት በእግዚአብሔር ፊት ደርሷል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እንዲህም አለኝ፦ ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ! እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቶአል፤ ለድኾች የምታደርገውም ምጽዋት ታስቦልሃል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 “ቆርኔሌዎስ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 10:31
14 Referencias Cruzadas  

“ሂድ፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ በዕ​ድ​ሜህ ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤


ወደ ካህኑ ወደ አሮን ልጆች ያመ​ጣ​ዋል፤ ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄ​ቱና ከዘ​ይ​ቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ነጩ​ንም ዕጣን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


ካህ​ኑም ከቍ​ር​ባኑ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውን ይወ​ስ​ዳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ነው።


ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ መታ​ሰ​ቢ​ያው ለእ​ርሱ እፍኝ ሙሉ ይዘ​ግ​ናል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ እር​ሱም የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነው።


መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ዘካ​ር​ያስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ ጸሎ​ትህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፤ ሚስ​ትህ ኤል​ሣ​ቤ​ጥም ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ዮሐ​ንስ ትለ​ዋ​ለህ።


ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የዛሬ አራት ቀን በዘ​ጠኝ ሰዓት በዚች ሰዓት በቤቴ ስጸ​ልይ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብስ የለ​በሰ አንድ ሰው በፊቴ ቆሞ ታየኝ።


አሁ​ንም ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በባ​ሕር አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት የሚ​ኖ​ረ​ውን ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ፤ እርሱ መጥቶ የም​ት​ድ​ን​በ​ትን ይነ​ግ​ር​ሃል።


ወደ​እ​ር​ሱም ተመ​ል​ክቶ ፈራና፥ “አቤቱ፥ ምን​ድን ነው?” አለ፤ መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ጸሎ​ት​ህም ምጽ​ዋ​ት​ህም መል​ካም መታ​ሰ​ቢያ ሆኖ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐር​ጎ​አል።


ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበ​ዛ​ል​ኝ​ማል፤ የመ​ዓዛ ሽታና የተ​ወ​ደደ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ስጦ​ታ​ች​ሁን ከአ​ፍ​ሮ​ዲጡ ተቀ​ብዬ አሟ​ል​ቻ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱ​ሳ​ንን ስለ አገ​ለ​ገ​ላ​ችሁ፥ እስከ አሁ​ንም ስለ​ም​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸው ያደ​ረ​ጋ​ች​ት​ሁን ሥራ፥ በስ​ሙም ያሳ​ያ​ች​ሁ​ትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመ​ፀኛ አይ​ደ​ለ​ምና።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos