ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።
ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
ባለማቋረጥ ጸልዩ፤
ዘወትር እንዲጸልዩ፥ እንዳይሰለቹም በምሳሌ ነገራቸው።
እንግዲህ ከዚህ ከሚመጣው ሁሉ በጸሎታችሁ ማምለጥ እንድትችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እንድትቆሙ ሁልጊዜ ትጉ።”
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ ለጸሎት ትጉ።
በጸሎትና በምልጃ ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ ከዚህም ጋር ስለ ቅዱሳን ሁሉ ለመጸለይ ሁልጊዜ ትጉ፤
በምስጋና እየተጋችሁ ለጸሎት ፅሙዳን ሁኑ።
ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፤
ጸሎቷንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ፥ ካህኑ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር።