1 ሳሙኤል 22:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ ጌታዬ ሆይ” ብሎ መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፤ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ፤ እንግዲህ ስማ” አለው። አቢሜሌክም፣ “ዕሺ ጌታዬ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፤ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ፤ እንግዲህ ስማ” አለው። አቢሜሌክም፥ “እሺ ጌታዬ” ብሎ መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም፥ “የአሒጡብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለው። አቤሜሌክም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ የአኪጦብ ልጅ ሆይ፥ እንግዲህ ስማ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ጌታዬ ሆይ ብሎ መለሰ። |
የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፌቡስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሥ ዳዊትም፥ “ሜምፌቡስቴ ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ አገልጋይህ” አለ።
ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቤሜሌክን፥ በኖብም ያሉትን ካህናት፥ የአባቱን ልጆች ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ሁላቸውም ወደ ንጉሡ መጡ።
ሳኦልም፥ “አንተ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለትህብኝ? እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፤ ዛሬም እንደ ተደረገው ጠላት ሆኖ ይነሣብኝ ዘንድ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ ጠየቅህለት” አለው።
ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ብላቴኖች፥ “ብንያማውያን ሆይ! እንግዲህ ስሙ በእውነት የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ መቶ አለቆችና ሻለቆች ያደርጋችኋልን?