ዳዊትም፥ “እኔ በፊትህ ሞገስን እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፤ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይቃወም አይወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ እኔ እንዳልሁት በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ያህል ቀርቶአል” ብሎ ማለ።
1 ሳሙኤል 20:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም ዳዊትን፥ “ነፍስህ ምን ትፈልጋለች? እኔስ ምን ላድርግልህ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንም ዳዊትን፣ “እንዳደርግልህ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር አደርግልሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንም ዳዊትን፥ “እንዳደርግልህ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር አደርግልሃለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም “አንተ የምትፈልገውን ሁሉ አደርግልሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም ዳዊትን፦ ነፍስህ የወደደችውን ሁሉ አደርግልሃለሁ አለው። |
ዳዊትም፥ “እኔ በፊትህ ሞገስን እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፤ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይቃወም አይወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ እኔ እንዳልሁት በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ያህል ቀርቶአል” ብሎ ማለ።
ዳዊትም ዮናታንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በንጉሥም አጠገብ ለምሳ አልቀመጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እንድሸሸግ አሰናብተኝ ።