ብላቴናውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ያልሁት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ።
1 ሳሙኤል 20:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውም ዮናታን ፍላጻውን ወደ ወረወረበት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮናታን፥ “ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው” ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁም የዮናታን ፍላጻ ባረፈበት ስፍራ እንደ ደረሰ፤ ዮናታን ጠራውና፣ “ፍላጻው ካንተ ወዲያ ዐልፎ የለምን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁም የዮናታን ፍላጻ ባረፈበት ስፍራ እንደ ደረሰ፤ ዮናታን ጠራውና፥ “ፍላጻው ካንተ ወዲያ ዐልፎ የለምን?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ልጅ ፍላጻው ባረፈበት ቦታ በደረሰ ጊዜ ዮናታን “ፍላጻው አልፎህ ሄዶአል! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውም ዮናታን ፍላጻውን ወደ ወረወረበት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮናታን፦ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ። |
ብላቴናውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ያልሁት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ።
ዮናታንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አትቈይ” ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ፤ የዮናታንም ብላቴና ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ።