ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
1 ሳሙኤል 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሠዋውም ሰው፥ “አስቀድሞ እንደ ሕጉ ስቡ ይጢስ፤ ኋላም ሰውነትህን ደስ የሚያሰኛትን ትወስዳለህ” ቢለው፥ እርሱ፥ “አይሆንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ ካልሆነም በግድ አወስደዋለሁ” ይለው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም፣ “በመጀመሪያ ሥቡ ይቃጠል፤ ከዚያ በኋላ የምትፈልገውን ትወስዳለህ” ቢለው እንኳ አገልጋዩ፣ “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ አለዚያ በግድ እወስዳለሁ” ይለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውየውም፦ “አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት፥ ከዚያም በኋላ ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ያህል ትወስዳለህ” ቢለው፥ እርሱ፦ “አይሆንም፥ አሁን ልትሰጠኝ ይገባል፤ ካልሆነ ግን በግድ እወስዳለሁ!” ይለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም “በመጀመሪያ ስቡን ያቃጥሉትና ከዚያ በኋላ የፈለግኸውን ትወስዳለህ” ቢለው፥ የካህኑ አገልጋይ “አይሆንም! አሁኑኑ ስጠኝ! እምቢ ብትል ግን በግድ እወስዳለሁ!” ይለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም፦ አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት ኋላም ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ትወስዳለህ ቢለው፥ እርሱ፦ አይሆንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፥ እንቢም ብትል በግድ እወስደዋለሁ ይለው ነበር። |
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው።
እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።
የዳንም ልጆች እንዲህ አሉት፥ “የተቈጡ ሰዎች እንዳያገኙህና ነፍስህም፥ የቤተ ሰቦችህም ነፍስ እንዳይጠፋብህ፥ ድምፅህ በእኛ መካከል አይሰማ።”
ደግሞም ስቡ ሳይጤስ የካህኑ ልጅ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።