La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ አወ​ጣሁ፤ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ፥ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ሁም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ’ አላ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብጻውያን እጅ ይጨቍኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብፃውያን እጅ ይጨቁኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፦ ‘እናንተን እስራኤልን ከግብጽ አወጣኋችሁ፤ ከግብጽ ኀይልና ከሚጨቊኑአችሁ መንግሥታት ሁሉ ጭቈና አዳንኳችሁ’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልንም ልጆች የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁ፥ ከግብጻውያንም እጅ ከሚያስጨንቁአችሁም ነገሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 10:18
7 Referencias Cruzadas  

በእ​ነ​ርሱ እጠራ ዘንድ፥ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸው ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


በሚ​ገ​ፋ​ች​ሁም ጠላት ላይ በም​ድ​ራ​ችሁ ወደ ሰልፍ ስት​ወጡ በም​ል​ክት መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ትታ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ትድ​ና​ላ​ችሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከገ​ል​ገላ ወደ ቀላ​ው​ት​ም​ኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ወጥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ እሰ​ጣ​ች​ሁም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር አግ​ብ​ቻ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም፦ ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አላ​ፈ​ር​ስም፤


ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።