La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 7:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሮማ​ኖ​ች​ንም ሠራ፤ በአ​ንድ ጕል​ላት ዙሪያ በሁ​ለት ተራ፥ በአ​ን​ድም መር​በብ ላይ ሁለት ተራ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ለሁ​ለ​ተ​ኛው ጕል​ላት አደ​ረገ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም በምሰሶዎቹ ላይ ያሉትን ጕልላቶች ለማስጌጥ የእያንዳንዱን መረብ ዙሪያ የሚከብቡ ሮማኖች በሁለት ረድፍ ሠራ፤ ለሁለቱም ጕልላቶች ያደረገው ተመሳሳይ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ ያሉትን ጉልላቶች ለማስጌጥ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ። ለየአንዳንዱም ጉልላት እንዲሁ አደረገ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ ያሉትን ጉልላቶች ለማስጌጥ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ። ለየአንዳንዱም ጉልላት እንዲሁ አደረገ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሮማኖችንም ሠራ፤ በአንድ ጕልላት ዙሪያ በተራ ሁለት መቶ ሮማኖች ነበሩ፤ በአንድም መርበብ ላይ ሁለት ተራ ነበረ፤ እንዲሁም ለሁለተኛው ጕልላት አደረገ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 7:18
8 Referencias Cruzadas  

በአ​ዕ​ማ​ዱም ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መር​በብ ሥራ አደ​ረገ፤ አን​ዱም መር​በብ ለአ​ንዱ ጕል​ላት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም መር​በብ ለሁ​ለ​ተ​ኛው ጕል​ላት ነበረ።


በወ​ለ​ሉም አዕ​ማድ በነ​በ​ሩት ጕል​ላ​ቶች ላይ የሱፍ አበባ የሚ​መ​ስል ሥራ አራት ክንድ አድ​ርጎ ቀረጸ።


ሁለ​ቱ​ንም አዕ​ማድ፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ኩብ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሁለ​ቱን መር​በ​ቦች፥


የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፥ የና​ስም ጕል​ላት ነበ​ረ​በት፤ የጕ​ል​ላ​ቱም ርዝ​መት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው የናስ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበሩ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓምድ ላይ መር​በብ ነበ​ረ​በት።


ሁለት ቋዶ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ እንደ ተጐ​ነ​ጐነ ገመድ አድ​ር​ገህ ሥራ፤ የተ​ጐ​ነ​ጐ​ኑ​ት​ንም ቋዶች በፈ​ር​ጦቹ ላይ አን​ጠ​ል​ጥል።


ለል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም የተ​ጐ​ነ​ጐ​ኑ​ትን ቋዶች እንደ ገመድ አድ​ር​ገህ ከጥሩ ወርቅ ሥራ​ቸው።