ወገባቸውንም በማቅ ታጠቁ፤ በራሳቸውም ገመድ ጠመጠሙ፤ ወደ እስራኤልም ንጉሥ ገብተው፥ “ባሪያህ ወልደ አዴር፦ ሰውነታችንን አድነን አለህ” አሉት። እርሱም፥ “ገና በሕይወት አለን? ወንድሜ ነው” አለ።
ወገባቸውንም በማቅ ታጠቁ፥ በራሳቸውም ገመድ ጠመጠሙ፥ ወደ እስራኤልም ንጉሥ መጥተው፦ ባሪያህ ወልደ አዴር፦ ነፍሴን ትምራት ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎአል አሉት። እርሱም፦ ገና በሕይወቱ አለን? ወንድሜ ነው አለ።