ኢዮራምም፥ “ሰረገላ አዘጋጁ” አለ፤ ሰረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ሁለቱም በሰረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊውም በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት።
1 ነገሥት 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራዊቱን ሁሉ ሰበሰበ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበባት፤ እየጠበቃቸውም ተቀመጠ። ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ነበሩ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፤ ወጥተውም ሰማርያን ከበቧት፥ ወጓትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የወይን ተክል ቦታ ላይ አንድ ነገር ደረሰ፤ ቦታውም በኢይዝራኤል ውስጥ ከሰማርያ ንጉሥ ከአክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፥ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ንጉሦች ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፥ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡቴ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በኢይዝራኤል በሚገኘው በንጉሥ አክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ የራሱ ርስት የሆነ አንድ የወይን ተክል ቦታ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፤ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገሥት ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም። |
ኢዮራምም፥ “ሰረገላ አዘጋጁ” አለ፤ ሰረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ሁለቱም በሰረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊውም በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት።
ኢዩም ጋሻጃግሬውን ቢድቃርን እንዲህ አለው፥ “አንሥተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ጣለው፤ አንተና እኔ ጎን ለጎን በፈረስ ተቀምጠን አባቱን አክዓብን በተከተልን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይህን መከራ እንደ ተናገረበት እኔ አስባለሁና አንተም ታውቃለህና፤
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።