1 ነገሥት 1:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ይህ ነገር ከጌታዬ ከንጉሡ የተደረገ ነገር ነውን? ለአገልጋይህም ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ለምን አልነገርኸውም?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ከርሱ ቀጥሎ በንጉሥ ጌታዬ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን አገልጋዮቹን ሳያሳውቅ ይህ እንዲሆን ንጉሡ ፈቅዷልን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ይህ ነገር ከጌታዬ ከንጉሡ የተደረገ ነውን? ለባርያህም ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን አልነገርህምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ በዙፋንህ ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሚሆን ለባለሟሎችህ ሳታስታውቅ ይህ የአዶንያስ መንገሥ ጉዳይ አንተ ያደረግኸው ነገር ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ይህ ነገር ከጌታዬ ከንጉሡ የተደረገ ነውን? ለባሪያህም ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን አልነገርህምን?” |
ነገር ግን እኔን አገልጋይህን፥ ካህኑንም ሳዶቅን፥ የዮዳሄንም ልጅ በናያስን፥ አገልጋይህንም ሰሎሞንን አልጠራም።
ወደ ተራራውም ወደ ኤልሳዕ ደርሳ እግሮቹን ጨበጠች፤ ግያዝም ሊያርቃት መጣ፤ ኤልሳዕም፥ “ነፍስዋ አዝናለችና ተዋት፤ እግዚአብሔርም ያን ከእኔ ሰውሮታል፤ አልነገረኝምም” አለ።
እንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ እናንተን ግን ወዳጆች እላችኋለሁ፤ በአባቴ ዘንድ የሰማሁትን ሁሉ ነግሬአችኋለሁና።