1 ቆሮንቶስ 15:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞት መውጊያ ኀጢአት ናት፥ የኀጢአትም ኀይልዋ ኦሪት ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞት መንደፊያ ኀጢአት ነው፤ የኀጢአትም ኀይል ሕግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞት መንደፊያ ኀይል ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኀይል ሕግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤ |
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “እኔ እሄዳለሁ ትሹኛላችሁም፤ ነገር ግን አታገኙኝም፤ በኀጢኣታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበትም እናንተ መምጣት አይቻላችሁም” አላቸው።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋው በበደላችን መጠን የሆነብን አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ከሞቱ፥ እንግዲህ በእግዚአብሔር ጸጋ፥ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በሰጠን ሀብቱ ሕይወት በብዙዎች ላይ እንዴት እጅግ ይበዛ ይሆን?
የአንዱ ሰው ኀጢአት ሞትን ካነገሠችው በአንድ ሰው በደልም ሞት ከገዛን፥ የአንዱ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ የጸጋው ብዛትና የጽድቁ ስጦታ እንዴት እጅግ ያጸድቀን ይሆን? የዘለዓለም ሕይወትንስ እንዴት ያበዛልን ይሆን?