La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 14:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለሴት በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን መና​ገር ክል​ክል ነው፤ ሊማሩ ከወ​ደዱ ደግሞ በቤ​ታ​ቸው ባሎ​ቻ​ቸ​ውን ይጠ​ይቁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፥ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በቤተ ክርስቲያን መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንዳንድ ነገርን ማወቅ ቢፈልጉ ባሎቻቸውን በቤታቸው ይጠይቁ፤ በጸሎት ስብሰባ ጊዜ ሴት እንድትናገር ተገቢ አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 14:35
7 Referencias Cruzadas  

ተፈ​ጥ​ሮ​ዋስ አያ​ስ​ረ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ወንድ ግን ጠጕ​ሩን ቢያ​ሳ​ድግ ነውር ነው።


ሴት ካል​ተ​ከ​ና​ነ​በች ትላጭ ወይም ጠጕ​ር​ዋን ትቈ​ረጥ፤ ለሴት ጠጕ​ር​ዋን መቈ​ረጥ ወይም መላ​ጨት ውር​ደት ከሆነ ትከ​ና​ነብ።


ሴቶ​ችም በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ዝም ይበሉ፤ ሊታ​ዘዙ እንጂ ሊና​ገሩ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ምና፤ ኦሪ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከእ​ና​ንተ ብቻ ወጥ​ቶ​አ​ልን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እና​ንተ ብቻ ደር​ሶ​አ​ልን?


በስ​ውር የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ለመ​ና​ገር የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነውና።


እንዲሁም እናንተ ባሎች ሆይ! ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።