1 ቆሮንቶስ 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ሁሉ ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ይረዳል፤ ለሁሉም እንደ ወደደ ያድላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰው እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ ይሰጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ሁሉ ግን አንዱና ያው መንፈስ ያደርጋል፤ እንደፈቃዱም ለእያንዳንዱ ሰው ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ የሚያደርገው ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ እንደ ፈቀደ ለእያንዳንዱ ሰው የተለየ ስጦታን ይሰጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል። |
ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለ፥ “ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በስተቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገንዘብ ሊያደርግ ምንም አይችልም።
ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳልና፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የሚወለድ ሁሉ እንዲሁ ነው።”
አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው እንዲሁ ወልድም ለሚወድዳቸው ሕይወትን ይሰጣል።
ነገር ግን ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው፥ ሁሉም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ እንዲህ ሥርዐት እንሠራለን።
ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው ጸጋ ይኑር፤ ግብሩ እንዲህ የሆነ አለና፤ ግብሩ ሌላ የሆነም አለና።
እኛስ ወደ እናንተ እስክንደርስ ድረስ እግዚአብሔር በወሰነልን ሕግና ሥርዐት እንጂ፥ ከዐቅማችን አልፈን እጅግ አንመካም።
እግዚአብሔርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በመስጠት፥ በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአምራትም መሰከረላቸው፤ ነገራቸውንም አስረዳላቸው።