La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 11:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ላመ​ሰ​ግ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ ወደ ዝቅ​ተኛ እንጂ ወደ​ሚ​ሻል ግብር አት​ሄ​ዱ​ምና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚጐዳ እንጂ ለሚጠቅም ስላልሆነ፣ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ እያመሰገንኋችሁ አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ይህን ትእዛዝ ስሰጥ አላመሰግናችሁም፤ ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚሻል ሳይሆን ለሚከፋ በመሆኑ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምታደርጉት ክፉ እንጂ መልካም ነገር ስላልሆነ በዚህ አሁን በምሰጣችሁ ትምህርት አላመሰግናችሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚከፋ እንጂ ለሚሻል ስላልሆነ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ የማመሰግናችሁ አይደለም።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 11:17
14 Referencias Cruzadas  

“ወን​ድ​ም​ህን አት​በ​ድ​ለው፤ በል​ብ​ህም አት​ጥ​ላው፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ት​ነ​ቅ​ፍ​በ​ትን ንገ​ረው፤ ገሥ​ጸ​ውም።


ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መል​ካም ለሚ​ሠራ የሚ​አ​ስ​ፈሩ አይ​ደ​ሉም፤ ሹሞ​ችን እን​ዳ​ት​ፈራ ብት​ፈ​ልግ መል​ካም አድ​ርግ፤ እነ​ርሱ ደግሞ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘወ​ትር ታስ​ቡ​ኛ​ላ​ች​ሁና፤ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ትም​ህ​ርት ጠብ​ቃ​ች​ኋ​ልና።


እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ የም​ት​በ​ሉና የም​ት​ጠጡ ለጌ​ታ​ችን ቀን እን​ደ​ሚ​ገባ አይ​ደ​ለም።


በውኑ የም​ት​በ​ሉ​በ​ትና የም​ት​ጠ​ጡ​በት ቤት የላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ታስ​ነ​ቅ​ፋ​ላ​ች​ሁን? ነዳ​ያ​ን​ንስ ታሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁን? ምን እላ​ለሁ? በዚህ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለ​ሁን? አላ​መ​ሰ​ግ​ና​ች​ሁም።


መሰ​ብ​ሰ​ባ​ችሁ ለፍዳ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የተ​ራበ ቢኖር በቤቱ ይብላ፤ አት​ነ​ቃ​ቀ​ፉም፤ ሌላ​ውን ሥር​ዐት ግን መጥቼ እሠ​ራ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ሕዝቡ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ቢሰ​በ​ሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቋንቋ ቢና​ገሩ፥ አላ​ዋ​ቂ​ዎች፥ ወይም የማ​ያ​ምኑ ቢመጡ አብ​ደ​ዋል ይሉ​አ​ቸው የለ​ምን?


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ሁላ​ችሁ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ መዝ​ሙር አላ​ችሁ፤ ትም​ህ​ርት አላ​ችሁ፤ መግ​ለጥ አላ​ችሁ፤ በቋ​ንቋ መና​ገር አላ​ችሁ፤ መተ​ር​ጐ​ምም አላ​ችሁ፤ ሁሉም ለሚ​ታ​ነ​ጽ​በት ጥቅም አድ​ር​ጉት።


ሌሎች ልማድ አድ​ር​ገው እንደ ያዙት ማኅ​በ​ራ​ች​ንን አን​ተው፤ እርስ በር​ሳ​ችን እን​መ​ካ​ከር እንጂ፤ ይል​ቁ​ንም ቀኑ ሲቀ​ርብ እያ​ያ​ችሁ አብ​ል​ጣ​ችሁ ይህን አድ​ርጉ።


ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።