1 ዜና መዋዕል 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፍሎስ፥ አስሮን፥ ከርሚ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል በኩር የሮቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያዕቆብ ልጆች በኲር የሆነው ሮቤል አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ ተብለው የሚጠሩት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ ነበሩ። |
የአባቶቻቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስሮን፥ ከርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ትውልድ ናቸው።